ከኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ለቅዱሳን ፓትሪያርኮች፣ ለብጹአን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እና ለቅድስት ቤ/ክ የተላለፈ መልእክት



የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ
28/10/2019
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ
ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀሪዮስ
እጅግ የተከበራችሁ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበረ ፓትሪያርክ
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ


የተከበራችሁ ቅዱሳን ፓትሪያሪኮችና የተወደዳችሁ ብጹአን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት


ወንድማዊ ሰላምታችን ይድረሳችሁ፡

ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በኢትዮጵያ እየሆነው ያለው ነገር በከፍተኛ መጠን እያሳሰበኝ መሆኑን ለመግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ ሁኔታዎችን በቅርብ እየተከታተልን በ ኦሲፒ ሚዲያ ነ አማካኝነት በቤተ ክርስቲያኒቷ ልጆች ላይ እየደረሱ ስላሉ ጥቃቶች የተለያዩ ዜናዎችንና ዘገባዎችን እየሰራን ሲሆን የተባበሩትን መንግስታት ጨምሮ ወደ ተለያዩ የሰብአዊ መብት ተቋማት የሚላኩ የፊርማ ማሰባሰቢያዎችን እየሞላን እንገኛለን፡፡

እግዚአብሔር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን፣ አመራሯን እና ምእመናኗን ከዚህ ችግር እንድትወጡ ያበርታችሁ፡፡ ጌታችንና አምላካችን ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ፡፡ በኢትዮጵያም ላይ ሰላምና ብልጽግና እንዲመጣ ክብሩን ይግለጥ፡፡
እ.ኤ.አ በ2013 ለጸሃፊያችን ጆርጅ አሌክሳንደር በኢትየጵያ በመንበረ ፓትሪያርክ ላደረጋችሁለት አቀባበል እያመሰገንን በ ኢ.አ በ2016 እርሶን በህንድ በመንበረ ፓትሪያርኳ ኮታየም ኬርላ እርሶን /ብ.ወቅ. አቡነ ማትያስ/ በመቀበላችን የተሰማንን ደስታ ለመግለፅ ዳለን፡፡ሁሌም ከናንተ ጋር ነን፡፡ 

   
በክርስቶስ ሰላም


ጆርጅ ጆሴፍ

ሊቀ መንበር

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልልና በአካባቢዎቹ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ የኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ /Orthodox cognate pafe (OCP)/ ለተባበሩት መንግስታት፣ ለአሜሪካ መንግስት የሃይማኖቶች ነጻነት ተቋምና ለተለያዩ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሪፖርቶችን አቀረበ፡፡



በኦርቶዶክሳዊያን አንድነትና አለማቀፋዊ ትብብር ዙሪያ የሚሰራው የኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ አለማቀፋዊ ተቀባይነቱ ከፍተኛ በሆነው ድረ ገጹ theorthodoxchurch.info በተከታታይ የኢትዮጵያውያን ኦርቶዶክሳውያንን ጥቃት በመዘገብ ለአለም ኦርቶዶክሳዊያን ማህበረሰብ በማሳወቅ  ላይ የሚገኘው  የኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ በዚህ ሳምንት የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ  ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ የአለም የሰብአዊ መብት ተቋማት የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚተነትን ሪፖርት ማስገባቱን የተቋሙ ሰክሬተሪያት ጂኦርጅ አሌክሳንደር ዛሬ ለ ተቋሙ የአማርኛ አገልግሎት OCPamharic ተናግረዋል   


The Office of the United Nations High Commissioner for Human Rights

President of the Russian Federation 

Prime Minister of Hungary

Chancellor of Germany

African Commission on Human and Peoples’ Rights

The U.S. Commission on International Religious Freedom

Organization for Security and Co-operation in Europe (OSCE)

UNESCO

Conference of European Churches

Churches Together in England

The Archbishop of Canterbury 

The Anglican Communion

Lutheran World Federation

Global Christian Forum

Release International

International Christian Concern

Christian Solidarity International

The Voice of the Martyrs

Justice Revival

Christian Solidarity Worldwide

Stefanus Alliance International

Human Rights Watch

Amnesty International

በትናንትናው እለት ቅዱስ ሲኖዶስ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ለሰማዕታቱ ጸሎተ ፍትሃት ማካህዱ የሚታወስ ነው፡፡