የኦርቶዶክስ የአንድት ገፅ /OCP/ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ

theorthodoxchurch.info
መግቢያ
የአለም አብያተክርስቲያናት በአንዲት ፣ሃዋርዊት ና አለምአቀፋዊት አንድነት ውስጥ ሣይከፋፈሉ ና ሣይነጣጠሉ ለመቆየት የታደሉት ከግማሽ ሺህ ዘመን ላልበለጠ ጊዜ ነበር።
አብያተክርስቲያናቱ ለ400 አመታት የገጠማቸውን የሠማዕትነት ዘመን አልፈው የክርስትናው ሀይማኖት በስፋት መግለጥ ፣ማብራራት ፣ ማስተማር ና መመርመር /ማመስጠር/ በጀመሩበት ዘመን ምንፍቅና ፣ ልዩልዩ የአስተምህሮ ልዩነት ፣ አለማዊ ፍልስፍና ቅየጣ እንዲሁም ፈተናዎች የክርስቶስ ቤተከርስቲያንን ያናውጣት ጀመር፡፡ በዚያ ዘመን እነዚህን ችግሮች ቢቻል ለመፍታት ባይቻል የችግሩን አካላት ለመለየት የተለያዩ አለምአቀፍ ጉባዔዎች ተካሂደዋል፡፡ ከነዚህ መካከል 4ቱ ጉባኤያት ይጠቀሳሉ፡፡ 3ቱ በእሪየንታል /የተዋህዶ/ ና ምሥራቅ ኦርቶዶክስ ና የካቶሊክ አብያተክርስቲያናት ተቀባይነት ሲኖራቸው 4ተኛው እና የመከፋፈል ምክንያት የሆነው ጉባዔ ግን በኦሪየንታል/የተዋህዶ / አብያተክርስቲያናት ተቀባይነት ያላገኘና ከምስራቅ /የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ና የካቶሊክ / አብያተክርስቲያናት ጋር በመወጋገዝ ያለያየ ና አብያተክርስቲያናት የተከፋፈሉበት ነበር፡፡
ይህ ዘመን ካለፈ በሗላ እጅግ በርካታ መከፋፈሎች ና ግጭቶች በተመሣሣይ ሁኔታ ደግሞ ወደ አንድነት ለመምጣት የሚደረጉ ጥረቶችም በዚሁ መልኩ ቀጥለዋል፡፡
 በተለይም በሁለቱ የኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት መካከል በተከታታይ የተደረጉ ይፋዊ ና ህቡዕ ውይይቶች አብያተክርስቲያናቱ እንዲቀራረብ ና አንድ የመሆን የመሆን ስሜቶች የተፈጠሩበት ወቅት ነበር፡፡
ለአብነትም 7ቱን የነገረ መለኮት ውይይቶች ማንሳት ይቻላል፡፡ እነሱም
1/ አርሁስ ፣ ዴንማርክ /ከነሃሴ 11 - 15 1964/
2/ ብሪስተል ፣ ኢንግላንድ /ከነሃሴ 25 - 29 1967/
3/ ጄኔቫ ፣ ስዊዘርላንድ /ከነሃሴ 16 - 21 1970/
4/ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ /ከጥር 22 - 23 1971/
5/ አባ ቢሾይ ገዳም ፣ ግብፅ /1989/
6/ ቻምባዚ ፣ ስዊዘርላንድ /1990/
7/ ቻምባዚ ፣ ስዊዘርላንድ /1993/ በነገረ ክርስቶስ /Christology) ዙሪያ መግባባት የተደረሠበትና አውጣኪና ንስጥሮስን የሚያወግዟቸው መሆኑን ያስረገጡበት ና ለመቀራረቦች በር የከፈተው ጉባኤ )
* ሁሉም አቆጣጠሮች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነው፡፡
ስለሁለቱ የኦርቶዶክስ ቤተሠቦች ይህን ያሀል ካየን ስለ የኦርቶዶክስ አንድነት ገፅ/OCP/
አመሠራረት ና ሌሎች ጉዳዮች በሚቀጥለው ክፍል እናነሣለን፡፡


No comments:

Post a Comment