የኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ ማህበር አመሰራረት


የኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ ማሀበር የኦርቶዶከሰ እምነትንና አንድነትን ለማስተዋውቅ በህንድ ሃገር በTravancore-Cochin Literary, Scientific and Charitable Societies Registration Act of 1955 መሰረት  እ.ኢ.አ በሰኔ/ሐምሌ 2007 ወሰን የለሽ ኦርቶዶከስ በሚል ስያሜ ተመሰረተ፡፡ በ2010ም ስሙን አሁን ወደሚጠራበት የኦርቶዶክስ አንድነት ገጽ ለወጠ፡፡
ተቋሙ ለምስራቃዊያንና ለኦሪየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት እኩል ትኩረት የሚሰጥ ሲሆን ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት የሐዋሪያትና የቅዱሳን አባቶችና እናቶች እምነት የነበረችው የአንዲት ቅድስት ክብርት አለማቀፋዊት(ካቶሊካዊት)ና ሃዋሪያዊት የሆነች የክርስቶስ ቤተ ክርሰቲያን አካላት ናቸው ብሎ ያምናል፡፡ መሪ ቃሉም የተባበሩት የኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ምስክር የሆነውም በዚህ መነሻነት ነው፡፡
ተቋሙ አስቀድሞ ለሁለቱ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የዜና ምንጭ ሆኖ ማገልገልን አላማው አድርጎ በሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበርና ጸሐፊ ሲመራ የነበረ ሲሆን በ2010 እ.ኤ.አ ግን ከስያሜ ለውጥ ባሻገር የአደረጃጀት ለውጥ በማድረግ 10 አመራሮች ባሉት ቦርድ መመራት ጀመረ፡፡ እንደ አንድ ህጋዊ ተቋምነቱ በየሶስት አመቱ የሚመረጥ አንድ አንድ መራሂ፣ ሊቀ መንበር፣ ምክትል ሊቀ መንበር፣ ጸሐፊና አምስት አባላት ያሉት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያለው ሲሆን ከሱ በታች ደግሞ ኦሲፒ ፋውንዴሽን፣ የመልዕክተኞች ጉባኤ፣ ጽህፈት ቤቱ፣ መምሪያዎችና የታዛቢዎች ጉባኤ በቅደም ተከተል አሉት፡፡
ተቋሙ የዜናና ጋዜጠኝነት፣ የጥናትና ምርምር፣ የማህበራዊ ሰብአዊ ድጋፎች፣ የጉብኝትና ውይይቶች፣ የዕውቅና አሰጣጥ፣ ንቅናቄዎችን የማዘጋጀትና ኦርቶዶክሳዊ ልኡካንን የመደገፍእንቅስቃሴዎችን ያካሂዳል፡፡
የተቋሙ መልክተኞች በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የኢርዶከስ አብያተ ክርስቲያት መሪዎች ጋር ተገናኝተው በአላማው ዙሪያ ተወያይተው  አወንታዊ ምላሾችን ከማግኘት ባሻገር የመታሰቢያ ሥጦታዎችን አበርክተዋል፡፡ ለአብነት ያህልም በፌብሩዋሪ 2008 የእንግሊዝ የኮብቲክ ኦርቶዶከስ ሊቀ ጳጳስ አባ ሱራፌል/ሴራፒም/ን ና ልኡካኑን፣ በ2010ና 2011 ከሶሪያ ኦርቶዶከስ ቤተክርስቲያን ተወካዮችና በ2015 ከቅዱስ ፓትሪያሪኩ ብፁዕ ወቅዱስ ሞራን ሞር ኢግናጢዮስ ዘካ ጋር፣ በ2013 ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስና ከወቅቱ የቤተክርስቲያኗ ልማትና ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሳሙኤል ጋር፣ በተመሳሳይ በዛው አመት  ከግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የአክሱም ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ጋር በ2014 ከኦሪየንታል አብያተ ክርስቲየናት ተወካዮች ጋር በህንድ፣ በ2015 ከህንድ ኦርቶዶክስ ፓትሪያሪክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስሊዮስ ጳውሎስ 2ኛ እንዲሁም በ2015 ከሲሪዮ ኦርቶዶክሲ ፍራንክፎን ቤተክርስቲያን መሪ ከብፁዕ ሞር ማሪያም ፊሊጶስ ጋር ተገናኝተዋል