ሳምንቱን በአርብ

                                                                     
ከ http://theorthodoxchurch.info/blog/news/ የተወሰዱ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አንኳር ዜናዎች

  • ሰርቢያ /መጋቢት 18 2011/   የሰርቢያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ  ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኤራንጂ በሰሜን አትላንቲክ ድርጅት /NATO/ ግድያ የተፈፀመባቸው የሰርቢያውያን መታሰቢያ ሥርዓት ቅዳሴ መርተዋል። ቅዱስነታችው በመታሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ ‘’ አባት ሃገራችንን እንጠብቃት፥ ያለን ብችኛ ጥንካሬም አንድንታችን ብቻ ነው።’’ ብለዋል።  


  • ሶሪያ /መጋቢት 18 2011/  የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ  ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኢግናጢዮስ ኤፍሬም II የብስራተ ድንግል ማርያምን በዓልና የሱቦሮ ቲቪ/SUBORO TV/ን የምረቃ በዓል ቅዳሴ መሩ። ቅዱስነታችው በዕለቱ በሰጡት ቃለ ምዕዳን ላይ “ከድንግል ማርያም በጌታ መታመንንና ሰማያዊ መልእክትን ለመክራ የሚያበቃን ቢሆንም እንኳን ምቀበልን ልንማር ይገባል።” ካሉ ብኋላ በመላው አለም ለሚገኙ የሶሪያ ኦርቶዶክሳዊያን በቴሌቪዠን ስርጭቱ መጀመር የእንኳን ደስ አላችሁ  መልእክታችውን አስተላልፈዋል።


  • አውስትራሊያ /መጋቢት 17 2011/  በአውስትራሊያ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሰታሊያኖስ አረፉ።



  • እንግሊዝ /መጋቢት 13 2011/ በእንግሊዝ የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ  ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንጋሊዎስ የእንግሊዝ የቤቶች ጉዳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃሉን ትርጉም በማዛባት ለክርስቲያን ኢራናዊያን ጥገኘነት ፈላጊዎች የሰጠውን ምላሽ ተቃወሙ። ብፁዕነታቸው ቢሮው ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን የማየት መብት የለውም ብለዋል።


ሙሉ ንግግራቸውን ለማዳመጥ https://www.premier.org.uk/News/UK/Home-Office-withdraws-refusal-of-asylum-seeker-after-criticising-the-Bible-in-rejection-letter
  • እስራኤል/መጋቢት 19 2011/    የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሪዩቫን ሪቫሊን ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት ምሪዎች ጋር የዮርዳኖስ ወንዝን ባሀረ ጥምቀት ጎብኙ። በጉብኝቱ ላይ የምስራቅና የኦርየንታል አብያተ ክርስቲያናት አባቶች ተሳትፈዋል።



የመጽሔት ግብዣ

https://basilica.ro/wp-content/uploads/2019/03/The-Good-to-Know-March-2019.pdf

የኦርቶዶክስ የአንድት ገፅ /OCP/ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ

theorthodoxchurch.info
መግቢያ
የአለም አብያተክርስቲያናት በአንዲት ፣ሃዋርዊት ና አለምአቀፋዊት አንድነት ውስጥ ሣይከፋፈሉ ና ሣይነጣጠሉ ለመቆየት የታደሉት ከግማሽ ሺህ ዘመን ላልበለጠ ጊዜ ነበር።
አብያተክርስቲያናቱ ለ400 አመታት የገጠማቸውን የሠማዕትነት ዘመን አልፈው የክርስትናው ሀይማኖት በስፋት መግለጥ ፣ማብራራት ፣ ማስተማር ና መመርመር /ማመስጠር/ በጀመሩበት ዘመን ምንፍቅና ፣ ልዩልዩ የአስተምህሮ ልዩነት ፣ አለማዊ ፍልስፍና ቅየጣ እንዲሁም ፈተናዎች የክርስቶስ ቤተከርስቲያንን ያናውጣት ጀመር፡፡ በዚያ ዘመን እነዚህን ችግሮች ቢቻል ለመፍታት ባይቻል የችግሩን አካላት ለመለየት የተለያዩ አለምአቀፍ ጉባዔዎች ተካሂደዋል፡፡ ከነዚህ መካከል 4ቱ ጉባኤያት ይጠቀሳሉ፡፡ 3ቱ በእሪየንታል /የተዋህዶ/ ና ምሥራቅ ኦርቶዶክስ ና የካቶሊክ አብያተክርስቲያናት ተቀባይነት ሲኖራቸው 4ተኛው እና የመከፋፈል ምክንያት የሆነው ጉባዔ ግን በኦሪየንታል/የተዋህዶ / አብያተክርስቲያናት ተቀባይነት ያላገኘና ከምስራቅ /የምሥራቅ ኦርቶዶክስ ና የካቶሊክ / አብያተክርስቲያናት ጋር በመወጋገዝ ያለያየ ና አብያተክርስቲያናት የተከፋፈሉበት ነበር፡፡
ይህ ዘመን ካለፈ በሗላ እጅግ በርካታ መከፋፈሎች ና ግጭቶች በተመሣሣይ ሁኔታ ደግሞ ወደ አንድነት ለመምጣት የሚደረጉ ጥረቶችም በዚሁ መልኩ ቀጥለዋል፡፡
 በተለይም በሁለቱ የኦርቶዶክስ አብያተክርስቲያናት መካከል በተከታታይ የተደረጉ ይፋዊ ና ህቡዕ ውይይቶች አብያተክርስቲያናቱ እንዲቀራረብ ና አንድ የመሆን የመሆን ስሜቶች የተፈጠሩበት ወቅት ነበር፡፡
ለአብነትም 7ቱን የነገረ መለኮት ውይይቶች ማንሳት ይቻላል፡፡ እነሱም
1/ አርሁስ ፣ ዴንማርክ /ከነሃሴ 11 - 15 1964/
2/ ብሪስተል ፣ ኢንግላንድ /ከነሃሴ 25 - 29 1967/
3/ ጄኔቫ ፣ ስዊዘርላንድ /ከነሃሴ 16 - 21 1970/
4/ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ /ከጥር 22 - 23 1971/
5/ አባ ቢሾይ ገዳም ፣ ግብፅ /1989/
6/ ቻምባዚ ፣ ስዊዘርላንድ /1990/
7/ ቻምባዚ ፣ ስዊዘርላንድ /1993/ በነገረ ክርስቶስ /Christology) ዙሪያ መግባባት የተደረሠበትና አውጣኪና ንስጥሮስን የሚያወግዟቸው መሆኑን ያስረገጡበት ና ለመቀራረቦች በር የከፈተው ጉባኤ )
* ሁሉም አቆጣጠሮች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ነው፡፡
ስለሁለቱ የኦርቶዶክስ ቤተሠቦች ይህን ያሀል ካየን ስለ የኦርቶዶክስ አንድነት ገፅ/OCP/
አመሠራረት ና ሌሎች ጉዳዮች በሚቀጥለው ክፍል እናነሣለን፡፡